በመጪው ክረምት ለሚካሄደው ሦስተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኞች ዝግጅት እየተካሄደ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ክረምት ለሚካሄደው ሦስተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኞች ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
የግብርና ሚኒስቴር በ2013/14 የምርት ዘመን ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተከሉ 6 ቢሊየን፣ ለጎረቤት ሃገራት 1 ቢሊየን እንዲሁም በማጓጓዝ እና በተለያየ ምክንያት የሚበላሹ ችግኞችን ለመተካት ተጨማሪ 1 ቢሊየን በድምሩ 8 ቢሊየን ችግኞች እየተዘጋጀ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል፡፡
ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ የችግኝ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን ሚኒስቴሩ ያስታወቀ ሲሆን የሚተከሉት ችግኞች ለደን ሽፋን፣ ለምግብነት እና ለቀርከሀ ቁሳቁስ ምርት የሚውሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ቀጣዩን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለማከናወን ለክልሎች ወደ 60 ሚሊየን ብር በጀት ይዘዋል።
ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች የተተከሉ ችግኞች ከ80 በመቶ በላይ እንደጸደቁ የግብርና ሚኒስቴር ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

One thought on “የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኞች ዝግጅት እየተካሄደ ነው”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *