“ኑ አዲስ አበባን እናልብሳት” በይፋ ተጀመረ# Ethiopia “ኑ አዲስ አበባን እናልብሳት “በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የአረንጓዴ አሻራየችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በጉለሌ እጽዋት ማዕከል ተካሄደ።በመርሀ-ግብሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ፣ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስፖርትቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሀ-ግብሩ አዲስ አበባ እናልብሳት ብለን በምርጫው እለት በአንድ እጅዴሞክራሲን በሌላ እጅ ደግሞ ችግኝ መትከል ጀምረናል ብለዋል።በዘንድሮ የክረምት ወራት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝለመትከል በእቅድ መያዙን የገለፁት ወ/ሮ አዳነች፤ ሁሉም ነዋሪዎች፣የፌደራል እና የሴክተር ተቋማት ከተማዋለኑሮ ምቹ እንድትሆን በየአካባቢው ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክትይገባል ብለዋል።የፌደራል እና የሴክተር ተቋማት፣ ለኤምባሲዎች እና ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንዲህም ሌሎች አካላትየችግኝ መትከያ ስፍራዎች መዘጋጀቱን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።ህብረተሰቡም ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ለነገው ትውልድአረንጓዴን ለማልበስ ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።በመርሀ-ግብሩ በእንግድነት ተገኝተው ችግኝ የተከሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርበአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የትብብር እና የአንድነት እንቅስቃሴ ለክልሎች ምሳሌ መሆኑን ጠቁመዋል።በዘንድሮ የክረምት ወራት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 7.5 ሚሊየን ችግኝለመትከል በእቅድ ከተያዘው በተጨማሪ በሰኔ 14 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ጎን ለጎን 2 ነጥብ 58 ሚሊየንችግኞች መትከል መቻሉን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል።# ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *